መቱ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ንቅናቄ ኮንፈረንስ አካሄደ፡፡ የህዝብ ንቅናቄ መድረኩ የተካሄደው የመቱ ዩኒቨርሲቲን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት የማክበረሰብ ሚና በሚል መሪ ቃል ነው፡፡ በዚህ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ላይ ከኢሉ አባቦር ና ቡኖ በደሌ ዞኖች ከተውጣጡ የተለያየ ባለድረሻ አካላት፣ የዩኒቨርሲቲው የበላይና መካከለኛ አመራር፣ መምህራንና ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዚህ የንቅናቄ ኮንፈረንስ ላይ መቱ ዩኒቨርሲቲ ከየት ወደየት በሚል ርዕስ የመዌ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በዚሁ መሰረት ለዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ዕድገት የማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ውሳን መሆኑን፤ ዩኒቨርሲቲው ለወደፊት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በትጋት እንደሚሰራና ህብረተሰቡም የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንድደግፍ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር መፍታት በሚችሉ ምርምሮችና የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ተጠይቋል፡፡