መ.ዩ፣ መስከረም 19፣ 2019 ዓ.ም
===========+===========
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ በቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ሰብሳቢነት የዩኒቨርሲቲውን የ2018 ዓ.ም የስራ ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሞ፣ የ2019 ዓ.ም የስራ ዕቅድን መርምሮ አፅድቋል።
ቦርዱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የስራ ስብሰባ በ2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ ዋና ዋና የስራ እንቅስቃሴዎች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የተለዩ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይትና ግምገማ አካሂዷል።
የ2018 ዓ.ም አፈፃፀሙን በመገምገምም መልካም አፈፃፀም ያስመዘገቡ የስራ ዘርፎች ማጠናከር፣ በአፈፃፀም ላይ የታዩ ክፍተቶችን መሙላት እና በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የስራ አቅጣጫዎችን በመለየት ላይ ትኩረት ተደርጓል።
በተጨማሪም ቦርዱ የዩኒቨርሲቲውን የ2019 ዓ.ም የስራ ዕቅድ በመርምር አፅድቋል። ዕቅዱ ዩኒቨርሲቲው ባለፈው ዓመት ከተማረባቸው ልምዶች በመነሳት የትምህርት፣ የምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ የተቋማዊ አቅም ግንባታ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራትን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ቦርዱ ከዩኒቨርሲቲው ዋና የስራ ዕቅድ በተጨማሪ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝን የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም መርምሯል። በዚህም የኢንተርፕራይዙ በ2018 ዓ.ም ያከናወናቸው ተግባራት፣ ያስመዘገባቸው ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተሻሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የተወሰዱ እርምጃዎች ተገምግመዋል።
በመጨረሻም የመቱ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ የ2019 ዓ.ም የስራ ዕቅድ በቦርዱ ተመርምሮ ፀድቋል። ዕቅዱ ኢንተርፕራይዙ የሚያመነጨውን ገቢ ለማሳደግ፣ የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል እና ለዩኒቨርሲቲው ዘላቂ ተቋማዊ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማጠናከር ያለመ አቅጣጫዎችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።
የስራ አመራር ቦርዱ በዚህ ግምገማና ዕቅድ ማፅደቅ ሂደት የዩኒቨርሲቲውን ተጠያቂነት፣ ውጤታማነት እና የተቋሙን የወደፊት የልማት አቅጣጫ ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።