መቱ ዪኒቨርሲቲ በዛሬዉ እለት የ10ኛ ዙር 2ኛ ምዕራፍ የተማሪዎች ምረቃ በዋናዉ ጊቢ በኦዳ ዶጊ የመመረቂያ አዳራሽ አከናውኗል። በዚህ የምረቃ ምዕራፍም 292 ወ. 182 ሴ. በድምሩ 479 የመጀመርያ ዲግሪ እንዲሁም 133 ወ. 19 ሴ. በድምሩ 152 የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በጤናና በተለያዩ የትምህርት መስኮች አስመርቋል።