መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያሰለጥን የነበረውን ተማሪዎች በደማቅ ስነ ስርዓት አስመረቀ።
መቱ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት መርሃ ግብር ያሠለጠናቸዉን ተማሪዎች ዛሬ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በደማቅ ስነስረዓት አስመርቋል። የምረቃ ስነ ስረዓቱን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚደንት ዶ/ር እንደገና አበበ ሲሆኑ ተመራቂዎች በዝህ አስቸጋሪ ወቅት ለምረቃ መብቃታቸዉ ለሌሎች ምሣሌ እንደሚሆን ገልፀዉ ተመራቂዎች ባገኙት እዉቀት በታማኝነት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ጥሪ አድርገዋል።
በምረቃ ስነ ስረዓቱ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዲሪ የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ እና የዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባል ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸዉ ተመራቂዎቹ በአላማ ፅናት ለዝህ ቀን በመድረሳቸዉን አመስግነዉ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ ባገኙት እዉቀትና ልምድ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ችግር መፍታት እንዳለባቸዉ ጠቁመዋል። የየቩኒቨርሲቲዉን የተለያዩ ስራዎች መጎብኘታቸዉን የተናገሩት ሚንስትር ዴታዉ ብዙ አብረታች ጅማሮዎችን እንዳዩና ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።